እምባዬ ለሻማዬ
~ማስታወሻነቱ ለኢትዮጵያው ብሌን ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ
መለስ ራእይ - ታሪክ
ማንነቱ
የህዝብ አለኝታ - ከጥንት
መሰረቱ
መበቅል ዓድዋ - ችግኝ
ወ'ደደቢት
ዓለምን ዙሮ - ከዚአም
ብሎ ገነት
ብሩክ ዘር - የሚልዮኖች
አባት
ብፁዕ ሐዋርያ - ሁለመና
ሂወት
ህያው አሻራ - መቸም
የማይሞት::
መለስ ለአገሩ ጥላ
- የኢትዮጵያ ዘማሪ
የገበሬው ባርያ - ለድሃው
ተቆርቋሪ
የወጣቶች ተስፋ - ለሴቶች
ተጠሪ
ለነፃነት ታጋይ - ለህዝቡ
ኣፍቃሪ
የሰላም ደራሲ - የሁላችን
መሪ::
ወይኔ ዛሬ ወይኔ
ዘንድሮ
የማይሰማ መርዶ ጣለብኝ
ጆሮ
ለሉዐላዊነታችን - ታጥቆ የቆመ
ከሂወቱ በላይ - እኛን
ያስቀደመ
ተርቦ ተጠምቶ - መንገድ
የከፈተልን
እውን ነው አሉ
- መለስ - ከሂወት
ተለየን:(
አንጀታችን ተቆረጠ፣ ልባችን
ተሰበረ፣ ደነግጥን…
እግዚኦ ወ'መሃረነ
- አገር ተዘረፈ!…
በፍፁም ቢያሎህ! ስምና
ወርቅ አስተምሩኝ
-
የሚገባውን - ሌላ ስም ላውጣለት!
ከብሮ ያስከበረሽ አንቺ
የኢትዮጵያ መሬት
ጨካኝ፣ ምስጋና ቢስ - ነጠቅሽን
በ'ውነት?
አንቺን ሲንከባከብ - እረፍት
ላልቀመሰ መሪ
ማን ይዘሽ ነው ዘንድሮ መለስን ምትቀብሪ?
ከብልሀተኛ ምሁራን - ከሊቅ
ሊቃውንቶቹ ንቁ
ምርጥ ልዩ ፍጥረት
- ከዓለማችን ፍሬዎች
እንቁ…
አገሬ አስተማሪ፣ ዶክተርሽ - ገበሬ
ምሃንዲሱ
አይደል የእግዚአብሔር ስጦታሽ - ሁለመናሽ
እሱ…
አሁን ማን ሊፅፍልሽ
ነው? - ማንስ
ሊያነብልሽ?
ማን ሊመራሽ ነው?
- ማንስ ሊያስተረጉምልሽ?
ወይኔ የኔ መሬት
- ዛሬ ጠለምሽን
በቃ!
ኣፍሪካም አጣች - አንጋፋው
ዜናዊ ጠበቃ…
ወይኔ ወይኔ - ወይኔ
ኢትዮጵያዬ በጣም
ተጎዳሽ
ገና በጥዋቱ አንድ
አይንሽ አጣሽ
ወዮ! በዪ እምዬ
- ለማይድነው ጠባሳሽ
የጥልቅ ሃዘኔ - የብላቴና
ፍቅር
ለጎልዳፋ ምላሴ - ልሳነ
ምስክር
እምባዬ ጎርፎ - ነገየለሽ
ፈሰሰ
መንጋዬን አፍርሶ - አካሌ
ደፈረሰ…
በለጋ ትከሻው - አገርን
አነግቦ ለኖረ
ማለፉ ስሰማ - መቆሚያዬ
ተሸረሸረ
ህልውናዬ በድሃው እምባ
ባዘቀ አካሌ
ደነዘዘ
ዕይታዬም ጨላለመ - ህሊናዬም
ፈዘዘ
መለሳችን ደከመኝ ሳትል - ስትንከራተት
ሌሊት ተቀኑ
እረፍት ነው ላንተ - የኣህጉር
ነው ሃዘኑ…
እኛ ግን አልቻልንም ተደራርቦብን
ማቅ ለበስን ሆዳችንም ባባ
ማቅረር አቃተን - ፈልቶ የሚገነፍል
እምባ
በሚጎርፈው ተንሳፈህ መንግስተ
ሰማያት ግባ
ስትሄድብን - ኣባትህን ተከትለህ
ሳንወድ ሸኘንህ - ገነትም ትመችህ
ከወላጆችህ ጋ ታገናኝህ - ከጓዶችህም ጋ ታኑርህ…
ይብላኝ ለኢትዮጵያ - የማይተካ
ልጅ ላጣች እናትህ
እኩል የምትደርሰኝ የራሴ
ስለ ሆንክ
የቀናችን ፀሓይ - አንተ
መች ሞትክ
የጨለማችን ሻማ - እያጎረስከን
ቀለጥክ…
በየትኛው ችሎታ - በምን
ልግለፅልህ
በየትኛው ኪነት - ግጥም
ልፃፍልህ
በየትኛው ቛንቛ - ቃሌ
ልመሰክርልህ
መግለፅ ያቅተኛል - እንዴት
እንደምወድህ
ልሳን ያጥርብኛል - ኣይኔ
ይንባልህ:(
ግን - አንበሳችን የዓይናች
ብሌን - የሂወታችን
ብርሃን
ገና ሳናመሰግንህ - በጎልማሳ
ዕድሜህ - ምነው
ተለየሀን?
ለመሆኑ ገነት እንዴት
አገኘሃት?
የፃድቃኖች በር ማን
ከፍቶ ጠበቀህ?
የደስታው ነጋሪት ማን
መታልህ?
ማን ገጠመ ማን
አቁዘመዘመ?
ከበሮ ማን ኣዘለ?
ማን ዘለለ?
ማን ዘመረ? ባንዴራህስ
ማን ተቀበለ?
ጥልቅ ሃዘኔ - የብላቴና
ፍቅር
የውስጣዊ ስሜቴን - ለመግለፅ
ስሞክር
'ተው አትንባ
አታልቅስ' - ጭራሽ
አትበሉኝ
ከሳምባዬ ጮኽ ብዬ!
- ለምን አላለቅስም
እንደ ነሓሴ ጎርፍ
- እምባዬም ለምን
አይፈስም…
አንዴ ልንባለት - በመለስ
ግዜ በእውን
ላልኖረው
የኢትዮጵያ አይኗና ልቧ
ስጦታዋን ላላወቀው
በማያብቡ በማይታመኑ - በኢሳቶች
ተቃጥሎ ብርሃን
ላጣው
በዘረኝነት ታፍኖ በጠራራው
ቀን ለጨለመው
ግድ የላቹም ልንባለት
- የንጋቱን ጎህ
ጸደል ላላየየው
እስኪ ልንባለት ለመጪው
ትውልድ - ገና
ላልታደለው
መንገድ ማን እንደከፈተለት
ለማያውቀው
የመለስን መሥዋዕትነት - ከመፃሕፍት
ለሚማረው
የሚለንየም ታሪክ ላመለጠው
ግን በድህነት ምትክ ልማት
ለሚወርሰው
አረ ለኛም ልምባ
- የኢትዮጵያን እድገት
ለውጥ ላየን
በላቡ ጥማታችን ላረካን
- በድካሙ የታንጉት
ጉርሻ ላበላን
ግን ያልታደልን - ምንሊክ
ገብተን እጅ
ላልነሳነው
ከባህር ማዶ ተመኝተን
ያላለልን - በሰው
አገር ያለነው
እሪ ብሎ ለሚያለቅሰው
ህዝቤ እኔም
ልንባለት
የመለስን ትንፋስ ለመመለስ
አልቅሶ ላልተሳካለት…
ለመለስ… እንኳን የዋህ
ልቤ - እግዚአብሔርም
አለቀሰለት
የአምላክ እምባ ዝናብ
ነው - ያውም
በርክቶ ጣለለት
ጀግናችን ብሩክ ነው
- ይሀው የህዝቡን
ሃዘንም አጠበለት
መቃብሩም ግርድፍ እንዳይሆንበት
በምራቁ አረጠበለት
ጥልቅ ሃዘኔ - የብላቴና
ፍቅር
የውስጣዊ ስሜቴን - ለመግለፅ
ስሞክር
እያያቹ ኮኮቡ ማጣቴን
ኣልቻል እያለኝ
'ግድ የለህም
አትንባ አትበሉኝ'
የ'መለስ ዜናዊ
ግድብ' ገና
ኣላለቀምና
የሚወደውን ህዝቡም ሶስቴ
ኣልበላምና
'ግድ የለህም
አትንባ አትበሉኝ'...
ቢለወጥ እምባዬ እሳት
ቢሆንልኝ
እኔም እንደ ሻማ
ተቃጥዬ ቀልጬ
ባለቁኝ
ክፍሌን ዘግቼ - ጥቁር ቀለም ነክሬ
ስሜቴን እንዲገልፅልኝ የተማፀንኩት
ብዕሬ
ሃዘኔን የሚገልፅ ቃላት ለመምረጥ
‘ሰዋስው ስፈትሽ' - መፃህፍት
ሳገላብጥ
ብተኛ፣ ብነሳ፣ ብራመድ፣ ብቀመጥ
ከቶ አደርኩኝ ላይሆንልኝ ለሚቀር
ያኔ እምባዬ ፈሰሰ ዳር እስከ
ዳር
በዚች በማላውቃት ምድር
አብሮኝ የሚያለቅስም ናፈቀኝ
ይሉኝታ ትቼም - ጮክ ብዬ አለቀስኩኝ
ሞራሌም ተነካ - ደረቴም መታሁኝ
የህዝቤን ሃዘን እጅጉ
ከበደኝ
እምባውን ትቼ እሳት
በመረጥኩኝ
መለስዬ ሳይዝናና - ኣባይ
ላይ ሳይዋኝ
ለመጨረሻ ማጣቴ - ፍፁም
ሰላም ነሳኝ
ኢትዮጵያ ያለመለስ - ማሰቡ
ደከመኝ
ክብሬ ተነጥቆ - ራቆቴ
ለወጣሁ
ልሳን ኣጥሮብኝ - ቃላት
ላጣሁ
በየትኛው መላ - ፍቅሬን
ልግለፅልህ
ኣይኖቼ ይቅለጡ - ልቤ
ይድማልህ
ልሳን ያጥርብኛል - ኣይኔ
ይንባልህ
አዎ እምባዬም ይገንፍል
- እንደ ፀበል
ይረጭ
ጥቁር ትልበስ እምዬ
- ፀጉሯንም ይላጭ
ተንከባሎ ይፍሰስ - ይነባልህ
ገና
ኢትዮጵያም ትምባ - ኣንተን
የሚተካ ኣልወለደችም'ና
ተዉኝ ተዉኝ - ተዉኝ
'ተው አትምባ
አትበሉኝ'
አይወጣልኝም ሃዘኑ - ጠልቆ
ገብቷል ከልቤ
ስር
መለስ ለድህነት - የቆፈሮውን
መቃብር
ድህነት እዛ ገብቶ
እስከሚቀበር
ሁሉም ኢትዮጵያዊ እስከሚያለብሰው
አፈር
ተዉኝ ተዉኝ - ተዉኝ
አትምባ አትበሉኝ::
ውድ የኣለማችን ዜጋ
- እንባችን ላየህ
የፍቅር ነው እንጂ
- የድክመት እንዳይመስልህ
እነዚህ ኣይኖች ገና
ያለቅሳሉ
የፈሰሰው ገድበው ሃይቅ
ይሰራሉ
የመለስን ራዕይ ሽቶው
ያደርሳሉ
ኣባይ፣ ጊልገል ግቤ፣
ተከዘን ይሞላሉ
በጥፍራቸው ቆፍረው ግብ
ያሳካሉ
መለስዬ-
ምዝገበ ቃላት ያጥርብናል
- ምስክራችን እምባችን
ነው…
ደህና ሁን ጀግናዬ
- ፈገግታህን ላናይ
ድምፅህ ላንሰማ
የተስፋችን ጭላንጭል የኢትዮጵያዊነታችን
ዜማ
የአንድነታችን መለዮ - ያስረከብከን
አርማ
ለዘላለም ትውለበለባለች - የሰቀልክልን
ውዲቷ ሰንደቅ
አላማ…
ላረግክልን ሁሉ 'በእጅጉ
እናመሰግናለን'
'እንኳን የኛ
ሆንክ' - 'እንኮራብሃለን'
እኛም ላንተ " በታላቅ ምስጋና እጅ እንነሳለን"
እንደ ፅኑ ቃልህ
- ቃላችን እንሰጣለን
ለሃግራችን እንደ ሻማ
በርተን - እንቀልጣለን
የወጠንከውና ያሳየሀን ራዕይ
- ሽቶው እናደርሳለን
ይሄው ባምላካችን ፊት
መሃላ እንገባለን::
ልጆችህ
ከ ዳንኤል ኢትዮጵያ
ነሓሴ 2012
ነሓሴ 2012